Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት እንተባበር- ከንቲባ ከድር ጁሀር

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት ሁሉም በየተሰማራበት የሥራ መስክ በሀገር ወዳድነትና በአንድነት በመቆም የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚጠበቅበት የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር አስገነዘቡ፡፡

” ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሐሳብ የሉዓላዊነት ቀን በድሬዳዋ አሥተዳደር ተከብሯል።

ከንቲባ ከድር በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሀገራችን በጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነት ሉዓላዊነቷ ለዘመናት ተከብሮ በዓለም አደባባይ ሰንደቋ በክብር መውለብለቡን ቀጥሏል ብለዋል።

ለሌሎች ሉዓላዊነት መከበርም በዓለም አደባባይ ታላቅ ዝናና ክብር የተጎናፀፈች ሀገር ናት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሀገር ሉዓላዊነት እና ክብርን ይበልጥ ከማፅናት ባሻገር የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ ተግባራት ከዳር እንዲደርሱ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

እስከ ሙሉ ነፃነቷ የተቀበልናትን ሀገር በላቀና በተሟላ ነፃነቷ ለመጪው ትውልድ ለማውረስ ያለመሰሰት እንሠራለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በዓሉን አስመልክቶም ለሀገር ክብር መስዋዕትነት የከፈሉ አካላትን የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ መከፈቱን የድሬዳዋ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version