Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ሰኒ ሮግስትሩፕ ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ሰላም መከበር ቁልፍ ሚና አላት አሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ሰላምና ጸጥታ በማስከበር ረገድ ቁልፍ ሚና መጫወቷን በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሰኒ ሮግስትሩፕ ተናገሩ።

አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ሰላምና ጸጥታን በተመለከተ በዓለም አቀፍና አኅጉራዊ መድረክ ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ዘርዝረዋል።

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት በተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስር በቀጣናዊ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላምን ለማስፈን ወሳኝ ሚና መጫወቱን  ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 1951 በኮሪያ ጦርነት ላይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተመራው ኃይል የነበራትን ወሳኝ ተሳትፎም አስታውሰዋል፡፡

ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሰላምና ጸጥታ መከበር ላበረከተችው አስተዋጽኦ በታሪክ የተመዘገበ ጉልህ ማሳያ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋትና የሚያጋጥሙ ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ሚናዋን በመወጣት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ አበርክቶ እንዳላትም አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version