አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለአራት ወራት የሚቆይ የማዕድ ማጋራት ጀመረ።
ድጋፉ በአዳማ ከተማ ለሚኖሩና የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆነ 200 አባወራዎች የሚደረግ ነው ተብሏል።
የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ቦጂያ መኮንን ድጋፉ የሚደረግላቸው በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው ብለዋል።
ድጋፉ ዱቄት፣ ዘይት፣ ሩዝና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ያካተተ መሆኑም ታውቋል።
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በከተማዋ 10 ሺህ ዳቦና እንጀራ በየቀኑ ሲያከፋፍል መቆየቱን የተናገሩት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ ለኮቪድ መከላከል የተለያዩ ምርምሮችና ፕሮጀክቶች በመሰራት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውን ለመደገፍም እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዚህም ለቀጣይ አራት ወራት ለ200 አባወራዎች የማዕድ ማጋራት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
የድጋፉ ተጠቃሚ የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች በበኩላቸው የኮቪድ ወረርሽኝ ተፅዕኖ አሳድሮባቸው መቆየቱን ተናግረው የተደረገላቸው ድጋፍ ተስፋ እንደሰጣቸው ገልፀዋል።
በአፈወርቅ እያዩ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

