Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢራን በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራን ከቀድሞው የሃገሪቱ አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዥ ጀኔራል ቃሲም ሱሌይማኒ ግድያ ጋር በተያያዘ በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥታለች።

የሃገሪቱ ጠበቆችም ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ 30 ሰዎች በቀድሞው አዛዥ ግድያ እጃቸው አለበት ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ቴህራን ዶናልድ ትራምፕ ተይዘው ይቅረቡልኝ ብላለች።

ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖልም እርሳቸውን በማቅረቡ በኩል ይተባበረኝ ስትልም ጠይቃለች።

የኢራኑ ጠበቃ አሊ አልቃሲምመርም ቴህራን ትራምፕን ለህግ ለማቅረብ ጥረቷን ትቀጥላለች ብለዋል።

እርሳቸውን በህግ የመጠየቁ ሂደትም ከስልጣን ከወረዱ በኋላም ይቀጥላል ነው ያሉት።

ከጉዳዩ ጋር ከኢራን በኩል ጥያቄ የቀረበለት ኢንተርፖል ግን እስካሁን ያለው ነገር የለም።

የኢራን የቀድሞው አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ሃይል መሪ ጀኔራል ቃሲም ባግዳድ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በድሮን በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸው ይታወሳል።

ምንጭ አልጀዚራ

Exit mobile version