Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሰላም ሚኒስቴር እና የሲቪክ ማህበራት ተወካይ የሰላም ግንባታና የልማት ተግባራትን ለማከናወን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስቴር እና የሲቪክ ማህበራት ተወካይ የተለያዩ የሰላም ግንባታና የልማት ተግባራትን ለማከናወን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና የብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን እና የፕሮጃይኒስት ሀገር በቀል ድርጅት ዳይሬክተር ወይዘሮ ነፃነት ተፈራርመዋል፡፡

በዚህ ወቅት ሚኒስትር ዲኤታዋ የፕሮጀክቱ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ተጠቃሚ ማድረግ እና የሰላም ባህል ግንባታን በማሳደግ አብሮነትን ማጠናከር ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ሰባት የሲቪክ ማህበራትን ወክለው የተገኙት ወይዘሮ ነፃነት መንግስቱ በበኩላቸው የሲቪክ ማህበራት በአስቸጋሪ ወቅት ለህዝብ ፈጥነው በመድረስ እና ከመንግስት ጋር በመቆም በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የፕሮጅክቱ መነሻ ካፒታል 8 ሚሊየን ብር ሲሆን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፕሮጀክቱ በመጀመሪያ ምዕራፍ የሚተገበርበት ወረዳ ሆኖ ተመርጧል፡፡

በቀጣይ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ይተገበራል መባሉን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version