አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሶስት ወራት 93 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 4 ሺህ 316 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ሃላፊ አቶ አሕመድ እንድሪስ እንዳሉት÷በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ባለሃብቶች በክልሉ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በትኩረት ተሰርቷል፡፡
በዚህ መሰረትም 93 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 4 ሺህ 316 ባለሃብቶች በተለያዩ ዘርፎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡
ባለሃብቶች በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ አአስፈላጊው ክትትት እየተደረገ መሆኑንም ሃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግተዋል፡፡
በፀሃይ ጉሉማ
በኦሮሚያ ክልል 93 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ
