Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

28 ሚሊየን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለአርሶ አደሮች ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 28 ሚሊየን ሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለአርሶ አደሮች መሰጠቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በፊንላንድ መንግስት ድጋፍ የሚተገበረውና በገጠር መሬት አስተዳደር ላይ የሚሰራው የራይላ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ መርሐ-ግብር ተከሂዷል፡፡

በዚህ ወቅትም የገጠር መሬት አስተዳደርን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት በርካታ አካላት ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

ፕሮጀክቱ የገጠር መሬት አስተዳደርንና አጠቃቀምን ለማዘመን እንዲሁም ፍትሃዊ የመሬት ተጠቃሚነትን በማስፈን ሒደት ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ ብሔራዊ የገጠር መሬት አስተዳደር የመረጃ ስርዓትን በመገንባት በ10 ክልሎች በሚገኙ 458 ወረዳዎች እየተተገበረ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 28 ሚሊየን 2ኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለአርሶ አደሮች መሰጠቱንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version