Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ቀን 260 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ 

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 12፣ 2012(ኤፍ ቢሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ቀን260 ሺህ  ሰዎች በኮሮና ቫይረስ  የተያዙ ሲሆን ይህም ከፍተኛው ቁጥር  ሆኖ   መመዝገቡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥ በአለም ዙሪያ አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከሩብ ሚሊዮን ማለፉን ድርጀቱ ጠቅሶ÷ ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ቀን የተመዘገበ ትልቅ  ቁጥር ነው ብሏል።

በወረርሽኙ ከፍተኛ  ጭማሪ ያስመዘገቡ ሀገራት አሜሪካ ፣ ብራዚል ፣ ህንድ እና ደቡብ አፍሪካ  ሲሆኑ በአለም ዙሪያ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥርም በአንድ ቀን 7ሺህ 360 መሆኑን ድርጅቱ አመላክቷል፡፡

ከዚህ በፊት በአንድ ቀን በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበው ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ መሠረት በአለም ዙሪያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ14 ሚሊዮን ማለፉ የሚታወስ ነው፡፡

 

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Exit mobile version