Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አየር መንገዱ ወደ ሞንሮቪያ ዳግም በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላይቤሪያ ሞንሮቪያ የመንገደኞች በረራውን ዛሬ ዳግም ጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣በኢትዮጵያ የላይቤሪያ አምባሳደርና ሌሎች የአየር መንገዱ የስራ ሃላፊዎችና እንግዶች ተገኝተዋል።

አየር መንገዱ በ2020 ላይ አቋርጦት የነበረውን በረራ ነው እንደገና ዛሬ ያስጀመረው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው÷ አየር መንገዱ ወደ ላይቤሪያ በረራ መጀመሩ የምጣኔ ሀብት፣ የቱሪዝምና ንግድ፣ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ያጠናክራል ብለዋል።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ባሉት 147 አውሮፕላኖች 140 ዓለም አቀፍና 22 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን የሚሸፍን ሲሆን እ.አ.አ በ2035 ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊየን ዶላር በማሳደግ በዓመት 67 ሚሊየን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ራዕይ ሰንቆ እየሰራም ይገኛል።

Exit mobile version