Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሊቨርፑል ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ13ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ሊቨርፑል በአንፊልድ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

ሊጉን በ31 ነጥቦች እየመራ የሚገኘው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ውኃ ሰማያዊዮቹን ያሸንፋል የሚሉ የቅድመ-ጨዋታ አስተያየቶችም ተበራክተዋል፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር የማሸነፍ ግምት የተሰጠው ቼልሲ 10 ሠዓት ከ30 ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ አስቶንቪላን ያስተናግዳል፡፡

እንዲሁም በተመሳሳይ ሠዓት ቶተንሃም ሆትስፐር ፉልሃምን፤ ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን በሜዳዎቻቸው ይገጥማሉ፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር እና ማንቼስተር ዩናይትድ ጨዋታዎቻቸውን የማሸነፍ ዕድላቸው ከፍ ያለ መሆኑም እየተነገረ ነው፡፡

 

Exit mobile version