አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)ከዴንማርክ የገንዘብ ሚኒስትር ኒኮላይ ሃልቢይ ዋመን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው በአየር ንብረት እና አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርምን አስመልክቶ ምክክር ማድረጋቸውን ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
እንዲሁም በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት እና የልማት አጀንዳ ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል፡፡