Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከንቲባ አዳነች በመዲናዋ ሙስናን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከነዋሪዎች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሙስናን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የጸረ ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ ከነዋሪዎች ጋር መወያየታቸውን አንስተዋል፡፡

ውይይቱ “ወጣቶችን ያማከለ የጸረ ሙስና ትግል የነገ ስብዕናን ይገነባል” በሚል መሪ ሃሳብ መካሄዱን ነው የገለጹት፡፡

በመድረኩ ለሁሉም የምትመችና ከሙስና ስጋት ነፃ የሆነች ከተማን መገንባት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ምክክር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

Exit mobile version