Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሚኒስትሮች በሰመራ ከተማ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚልና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

በጉብኝታቸውም በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ በተለያዩ ዞኖች የሥራ ጉብኝት እንዲሁም ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version