አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገቡ መሆናቸው ተገለጸ።
በዞኖቹ የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የኦነግ ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ መግባታቸውን እንደቀጠሉ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ አመልክቷል።
በዚህም በጎቡ ሰዮ፣ ጊዳ አያና፣ ኤባንቱ፣ ጉደያ ቢላ፣ ደገምና ወረ ጀርሶ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ካምፕ ገብተዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ ካምፕ እየገቡ መሆናቸው ይታወቃል።