አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል የህብረተሰብ ወኪሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ መጠናቀቁን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባዬ ኡጋቶ በሰጡት መግለጫ ÷10 የማህበረሰብ ክፍሎችን ወክለው የተገኙ 7 ሺህ 20 ተወካዮች ለጠቅላላ ጉባኤ የሚሳተፉ 320 ተወካዮችን መርጠዋል ብለዋል፡፡
የማህበረሰብ ተወካዮች የምክክር ሒደት መጀመሪያ የነበረው የመነጋገር ፍላጎት በሚገባ የተንፀባረቀበት መሆኑን አንስተዋል።
በአጀንዳ አሰባሰቡ ያልተገደቡ ውይይቶች መደረጋቸውን ጠቁመው÷ ተዓማኒና ሁሉም የተሳተፍበት እንደነበር አስረድተዋል፡፡
የ320ዎቹ ተወካዮች ምርጫም ክርክር ተደርጎበት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መከናነወኑን ነው የገለጹት፡፡
በቀጣዮቹ ቀናት የአጀንዳ መለየትና የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እንደሚካሄድም ተጠቅሷል፡፡
በአሸናፊ ሽብሩና መራኦል ከድር