Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያና ርዋንዳ ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) ከርዋንዳ አቻቸው ጁቬናል ማሪዛሙንዳ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ በወታደራዊ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version