አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ 422 ሺህ 842 ሰዎች ስልጠናውን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ የኢኒሼቲቩን አተገባበር ለመከታተል እና ለመደገፍ ለተቋቋመው ግብረ-ኃይል መመሪያ በሰጡበት ወቅት እንዳሉት÷ እስከ አሁን 104 ሺህ 460 ሰዎች ስልጠናውን አጠናቅቀው የምስክር ወረቀት ወስደዋል።
5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን የዲጂታል ክኅሎት ስልጠና እንዲወስዱ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በቅንጅት እየተሠራ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።