አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡
በስብሰባው የፕላን፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
ባቀረቡት ሪፖርትም የንብረት ታክስ በከተሞች ነዋሪ በሆነው ህዝብ መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚያሰፍን በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ እንደተዘጋጀ ገልጸዋል፡፡
የመንግስት አገልግሎትንና መገልገያ ቦታዎችን በተሻለ ጥራት ለማቅረብ እንዲሁም ለማደስና ቀጣይነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚወጣውን የኢንቨስትመንት ወጪ በንብረት ዋጋ ማደግ ምክንያት በሚጣል ታክስ አማካኝነት መሰብሰብ የሚያስችል በመሆኑ አዋጁ ተዘጋጅቷ ብለዋል፡፡
ምክር ቤቱ በስብሰባው የ14ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃል ጉባዔውንም በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን÷የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋል መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በየሻምበል ምህረት