Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ እየተመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ እየተመረቀ ይገኛል፡፡

የምረቃ መርሐ ግብሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

እንዲሁም ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ጨምሮ የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎችና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየክፍል ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናን ተገኝተዋል።

Exit mobile version