አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ፥ የጥምቀት በዓል የተለመደውን ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግ ከሃይማኖቱ አባቶች ጋር ተወያይተናል፡፡
ሁላችንም በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን እና የቱሪስት መስህብነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ተባብረን በጋራ እንስራ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::