Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጥምቀት የኅብረ ብሔራዊነት መገለጫ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተራ እና ጥምቀት በዓላት የኅብረ-ብሔራዊነት መገለጫ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ እና ድሬዳዋ አሥተዳደሮች ለከተራ እና ጥምቀት በዓላት የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞች መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የኅብረ-ብሔራዊነት መገለጫ የሆነው የጥምቀት በዓል የእኛነታችን መገለጫ ነው ብለዋል።

ጥምቀትን ስናከብርም ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቱን በማጎልበት፣ ኅብረ-ብሔራዊነቱን በማጠናከር፣ ለቱሪዝም ዘርፍ እድገት እና ለሀገር ገፅታ ግንባታ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ በማጉላት፣ ውብ እና ደማቅ በሆነ ሁኔታ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡

በተመሳሳይ የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የጥምቀት በዓል በቅርስነቱ በዩኔስኮ መመዝገቡ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ዕሴት ያደርገዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የከተራና የጥምቀት በዓላት የሰላም፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት ሁነት በመሆናቸው÷ በዓላቱን ስናከብር የድሬዳዋ እሴት በሆነው የአብሮነት እና የፍቅር ባህላችንን በጠበቀ መልኩ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንም ከንቲባዎቹ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version