Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የ5ኛ 5 ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ የጉባዔውን አጀንዳዎች መርምሮ በማጽደቅ ጉባዔውን ጀምሯል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የክልሉን የ2012 የአስፈጻሚ አካላት ዓመታዊ የአፈጻጸም ሪፓርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በክልሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት አበረታች እንደሆኑ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል፡፡

በዓመታት የተጓተቱ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ የቁሳቁስ እና ባለሙያ የማቅረብ ስራ እንደተከናወነ ጠቁመዋል።

ምክር ቤቱ እስከ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባዔው የ2012 ዓ.ም የአስፈጻሚ አካላት ሪፖርት ገምግሞ ከማጽደቅ በተጨማሪ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የኦዲት ዋና መስሪያቤት እንዲሁም የጽህፈት ቤቱን ሪፖርቶች ገምግሞ የሚያጸድቅ ሲሆን፣ በ2013 ዓ.ም በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ የተለያዩ አዋጆችንና የሚቀርቡ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

Exit mobile version