Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፈር ማዳበሪያ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፌዴራል መንግሥት ለ2017/18 የምርት ዘመን የተገዛ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ መሆኑን በክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ።

ለቀጣይ የምርት ዘመን ለክልሉ 1 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እንደሚያስፈልግ የገለጹት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አበራ ከደነው÷ የፌዴራል መንግሥት በግብርና ሚኒስቴር በኩል ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የምርት ዘመን የግብርና ግብዓት እጥረት ያጋጥማል የሚል ስጋት እንደሌለም ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በፌዴራል መንግስት ለቀጣይ የምርት ዘመን የሚሆን የተገዛ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሉ ብሎም መጋዘን ወደ ተዘጋጀላቸው ወረዳዎች መጓጓዝ መጀመሩንም አስታውቀዋል፡፡

ግብዓቱ ወደ ክልሉ በወቅቱ መግባት መጀመሩ ምርትና ምርታማነት መጨመር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አመላክተዋል፡፡

የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥምም ከሞዴል አርሶ አደሮች የኅብረት ስራ ማኅበራትና የምርምር ተቋማት ጋር በትብብር እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

Exit mobile version