አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መቀመጫቸውን በሀገር ውስጥ ያደረጉ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞች እና ከመገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ፌደራል ፖሊስ መረጃ መርና ማህበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል መርሕን የሪፎርሙ አካል አድርጎ ያከናወናቸውን ውጤታማ የወንጀል መከላከልና የወንጀል ምርመራ ሥራዎች ተመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም ተቋሙ ቴክኖሎጂዎችን በማበልጸግ የሠራቸውን ተግባራት ተዘዋውረው መመልከታቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ጋዜጠኞቹ በቀጣይ የፎረንሲክ ሳይንስ ኢንስቲትዩት የምርምር ልህቀት ማዕከልን እና የኢንተርናሽናል ፖሊስ ሊደርሽፕ ኢንስቲትዩት ፕሮጀክትን እንደሚጎበኙ ተጠቁሟል፡፡