አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የናሚቢያ አምባሳደር ምባፔዋ ሙቫንጓ እና በኢትዮጵያ የሲሼልስ አምባሳደር ኮንራድ ቪንሴንት ሜድሪች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮቾ ላይ መክረዋል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ የናሚቢያ አምባሳደር ምባፔዋ ሙቫንጓ ጋር ባደረጉት ውይይት÷ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና አቪዬሽን የትብብር መስኮች ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
በተመሳሳይ ከአምባሳደር ኮንራድ ቪንሴንት ጋር በነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያ ከሲሸልስ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና አህጉር አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡