Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አየር መንገዱ ቦይንግ 777ኤፍ እቃ ጫኝ አውሮፕላንን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777ኤፍ እቃ ጫኝ አውሮፕላንን መረከቡን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ የካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡

ዛሬ የተቀበልነው ቦይንግ 777ኤፍ እቃ ጫኝ አውሮፕላንም የካርጎ ጭነት አገልግሎት አድማሳችንን ለማሳደግ የራሱ አስተዋፅዖ ከማበርከቱም በተጨማሪ እያደገ የመጣውን የካርጎ አገልግሎት ለማስተናገድ የራሱ አስተዋፅዖ ይኖረዋልም ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የላቀ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠሉም ተነስቷል፡፡

በዚህም ይህ አዲስ የካርጎ አውሮፕላን አየር መንገዱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን የሚያግዙና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ተቋማት የሚለገሱ ቁሳቁሶችንም ወደ ሀገር ውስጥ ይዞ መምጣቱንም በትስስር ገጹ አስታውቋል።

Exit mobile version