Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በተሽከርካሪ መገልበጥ አደጋ የሁለት ሠወች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ ዙብአንባ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሞፈር ውሀ ጅረት አካባቢ እየተባለ ከሚጠራው ሥፍራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ አንድ ከባድና አንድ ቀላል ጉዳት ደረሰ፡፡

አደጋው ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት መዳረሻውን መሀልሜዳ ያደረገ ተሸከርካሪ መንገድ ስቶ በመገልበጡ የደረሰ ነው ተብሏል፡፡

ተጎጂዎች በደብረ-ብርሀን ሪፈራል ሆስፒታል እየታከሙ ሲሆን ፥ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version