Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

በቢሮው የቱሪዝም ልማትና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ፋንታሁን ታደሰ፤ በክልሉ የቱሪስት መዳረሻዎች ልማት ማስተርፕላን በማዘጋጀት የሀብት ልየታና ልማት ተግባር ሲከናወን ቆይቷል።

በተለይም የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን በማልማት የቱሪስቱ ቆይታን ለማራዘም የሚያግዙ መሰረተ ልማት የማሟላት ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ እንደነበረ አመልክተዋል።

በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሂደትም የባለሀብቱን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዙ የህግ ማዕቀፎች እንዲሻሻሉ መደረጉንም አስታውቀዋል።

የክልሉን የቱሪዝም መስህብ ከማስተዋወቅ አንጻር የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ቋሚ ቅርስ ሆኖ እንዲመዝገብ ማድረጉን በማሳያነት አስታውሰዋል።

ከባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተጨማሪ ድሬ ሼክ ሁሴን እና የሀረናን ጥብቅ ደን ለመስህብነት እንዲውሉ ለማስቻል እየተሰራ ነው ብለዋል።

በኢሉባቦር የሚገኘው ትልቁ የሶር ፏፏቴም ለቱሪስት ምቹ እንዲሆን የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተከናወነ ሲሆን በሌሎች አካባቢዎችም ሥራው ይጠናከራል ብለዋል።

ኢሬቻንና ሌሎች የህዝብ በዓላትን በማስተዋወቅ በሀገር ውስጥና በውጭ ቱሪስቶች ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ ሲሰራ መቆየቱን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version