አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባቡር ትራንስፖርቱን አቅም ማሳደግ የሚያስችል የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ መደረጉን የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) ገለፁ፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት÷ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱ ይፋ ተደርጓል፡፡
ስትራቴጂክ እቅዱ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርቱን የጭነት አቅም የሚያሳድግ እና አዳዲስ የትራንስፖርት ኮሪደሮችን መክፈት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በስትራቴጂክ እቅዱ የባቡር ትራንስፖርቱን ቀልጣፋ ማድረግ የሚያስችሉ ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎች ተግባራዊ እንደሚደረጉበት ጠቁመዋል፡፡
እቅዱ የሀገሪቱን የሎጂስቲክ ዘርፍ ለማሳለጥ ያግዛል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህም ኢኮኖሚውን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡