Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ130 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ቤቶች ለነዋሪዎች ተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ሸበሊ ከተማ ከ130 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ቤቶችን ለአቅመ ደካማ ወገኖች አስረከቡ፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት÷ ቤቶቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች አካል መሆናቸውን ገልጸዋል።

የመንግሥት ዋና ትኩረት የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ በመሆኑ መሰል ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version