አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የሴክተር ጉባዔ በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ÷ ከሁሉም ክልሎች የመጡ የትራንስፖርት ኃላፊዎች ሲመለሱ የዜጎችን ደኅነትና ተገቢ የትራንስፖርት አገልግሎት ስለመሰጠቱ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ ጉባዔው ለችግሮች መፍትሔ እያስቀመጥን ለመሄድ፣ ስኬቶችን አጠናክረን ለመሄድና ልምድ ለመለዋወጥ ይጠቅማል ብለዋል፡፡
በጉባዔው ላይ አቅጣጫ እንደሚሰጥ መናገራቸው የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡