Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም በሆሳዕና ከተማ ተመሰረተ።

የፎረሙ መመስረት ዐቢይ ዓላማ የክልሉን ሕዝቦች የእርስ በርስ መስተጋብር ከማጠናከሩም በላይ፤ ከመንግስት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችል መሆኑን የፎረሙ ሰብሳቢ ዳኛ ሞላ ጫኬቦ ተናግረዋል፡፡

የክልሉን ሕዝቦች አንድነት ለማስጠበቅ፣ ባህሎችና እሴቶች ለማጎልበትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፎረሙ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የፎረሙ አባላት በክልሉ የሚነሱ ጉዳዮችን በውይይትና በምክክር ለማስፈጸም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ሁሉንም የክልሉን ሕዝቦች በእኩልነት እና በታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውንም አረጋግጠዋል።

Exit mobile version