Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ካቢኔው ባካሄደው የ4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ስብሰባው የሀገሪቱን ዲፕሎማሲ ታሳቢ ያደረገ የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄን እና የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅቃሴ ለሚያጎለብቱ፣ ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ ላሉ፣ የዉጪ ምንዛሬ እያስገኙ ላሉ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎችን መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል።
Exit mobile version