Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ከ2 ሺህ 300 ሊትር በላይ ቤንዚን ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ 2 ሺህ 360 ሊትር በላይ ቤንዚን መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ስሙ ሰንጋ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን ወንጀል ፈፃሚ ግለሰቦቹ ከመንግስት የግብይት ስርዓት ውጭ ለመሸጥ እና ትርፍ ለማግኘት በማለም ቤንዚኑን እንደደበቁ ተገልጿል።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ቤንዚኑ በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በጀሪካን ተሸሽጎ መያዙን የገለጸው ፖሊስ፤ ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

ህብረተሰቡ በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Exit mobile version