Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምክር ቤቱ ሁለት የብድር ስምምነት አዋጆችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

ም/ቤቱ በልዩ ስብሰባው በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለፋይናንስ ዘርፍ ማጠናከሪያ የሚውል የብድር ስምምነትን ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል የተፈረመውንና ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማጽደቁ ተመላክቷል፡፡

አዋጆቹን አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራርያ ሰጥተዋል።

በዚህም የብድር ስምምነቶቹ የፋይናንስ ዘርፉን ለማጠናከር እና የመንግስት አገልግሎትን ለማሻሻል የሚውሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

Exit mobile version