Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከጨመረባቸው ሀገራት ቀዳሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከጨመረባቸው ሀገራት ቀዳሚ መሆኗ ተገልጿል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ቱሪዝም ዘርፍ እንዳስታወቀው÷ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተጎዳውን የቱሪዝም ዘርፍ በማነቃቃት ባለፉት 5 ዓመታት የዓለም አቀፍ ጎብኚዎቿ ቁጥር 40 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

በዚህም በአፍሪካ ባለፉት አምስት ዓመታት የጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከጨመረባቸው ሀገራት ቀዳሚ መሆን ችላለች፡፡

ሞሮኮ እና ግብጽ ደግሞ ኢትዮጵያን በመከተል 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን እንደያዙ የተባበሩት መንግስታት ቱሪዝም ዘርፍ የ2024 ሪፖርት ያመላክታል፡፡

ከዓለም ደግሞ ኳታር፣ ኤል ሳልቫዶር፣ አልቤንያ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ እና ኩራካዎን በመከተል ኢትዮጵያ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

Exit mobile version