አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በህንድ ኩምብ ሜላ ፌስቲቫል በተፈጠረ ክስተት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ሀዘኗን ገለጸች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በህንድ ኩምብ ሜላ ፌስቲቫል ላይ በሰዎች መብዛት ምክንያት ተፈጠረ ግርግር ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት በዚህ ከባድ ወቅት ከህንድ ህዝብ እና መንግስት ጎን መሆኑን ገልጾ፤ ለህንድ ህዝብና መንግስት መጽናናትንም ተመኝቷል።
በህንድ ፕራያጋራጅ በኩምብ ሜላ ፌስቲቫል በተፈጠረ ግርግር 15 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በርካቶች መጎዳታቸው ተነግሯል፡፡