Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የጎረቤት ሀገራት እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሀሳብ  ከትላንት  ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል።

በጉባኤ ላይ ለመታደም ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት የመጡ እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በጉባኤው መክፈቻ ላይ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

በዛሬው እለትም ከፍተኛ አመራሮች የእንጦጦ ፓርክን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በፓርኩ አስጎብኝዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

Exit mobile version