አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ መመረጣቸውን ምክንያት በማድረግ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩ በደስታ መግለጫ መልዕክታቸው የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ሆነው ለተመረጡት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አደም ፋራህም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የተመረጡት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር ለማድረስና የኢትዮጵያን ህልም እውን ለማድረግ በድጋሚ ዕድል ስላገኙ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት ርዕሰ መሥተዳድሩ፤ መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል።