Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትግራይ ክልል ከትምህርት ርቀው የቆዩ ሕጻናትን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል ስድስት ወረዳዎች ከትምህርት ገበታ የራቁ ሕጻናት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

በፕሮጀክቱ ተማሪዎቹን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ የትምህርት ቤት ምገባ፣ የሥነ ልቦናና የቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ጉኡሽ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ ፕሮጀክቱ ከትምህርት ገበታ የራቁ 64 ሺህ 650 ሕጻናት ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

ሕጻናቱን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ የተቀረጸው ይህ ፕሮጀክት ለቀጣይ ሦስት ዓመታት ይተገበራል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ከሕጻናት አድን ድርጅት የትግራይ ቅርንጫፍ በተገኘ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በጀት እንደሚተገበር የጠቆሙት ሃላፊው፤ ፕሮጀክቱ የትምህርት ተሳትፎ ለማጠናከርና ጥራትን ለማምጣት ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቱን ስኬታማ ለማድረግ የተቀናጀ የክትትል ሥራ እንደሚሰራ መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

Exit mobile version