Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትግራይ ክልል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል በሚገኙ አካባቢዎች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ዛሬ መጀመሩን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ኃላፊ ኢያሱ አብርሃ (ዶ/ር) እንደገጹሉት÷ ሥራው ለ20 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በዚህም 30 ሺህ ሄክታር መሬት እንዲለማ ይደረጋል።

በተለይም የተጎዱ ሥፍራዎችን መልሰው እንዲያገግሙ የማድረግ ዓላማ ያለው ነውም ብለዋል።

ሥራውን በጥራትና በፍጥነት ለማከናወን የሚያስችሉ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን የተናገሩት ደግሞ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሚኪኤለ ምሩፅ ናቸው።

ባለሙያዎች ሥራውን በቅርበት ለመምራትና ለመከታተል ወደየወረዳዎቹ ተሰማርተዋልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version