Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምእራብ ሸዋ ዞን ከ3 ሚሊየን በላይ የቡና ችግኝ ተተከለ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 21 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምዕራብ ሸዋ ዞን በተያዘው የክረምት ወቅት ከ3 ሚሊየን በላይ የቡና ችግኝ መተከላቸውን የዞኑ እርሻ፣ ቡናና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በጽህፈት ቤቱ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ጥራትና ግብይት የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ቶለሳ አራርሳ÷ችግኞቹ  በ740 ሔክታር መሬት ላይ መተከላቸውን ገልጸዋል ።

የቡና ችግኞቹ በሽታን ተቋቁመው ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የተሻሻሉ ዝርያዎች ናቸው ብለዋል።

በዞኑ 11 ወረዳዎች 3 ሚሊየን 201 ሺህ የቡና ችግኝ የተተከለ ሲሆን ÷12 ሺህ 33 አርሶ አደሮች በስራው ተሳትፈዋል ነው የተባለው።

የዳኖ ወረዳ አርሶአደር  ተሬሳ  ደጋጋ  በሰጡት አስተያየት ÷ በባለሙያ ምክር በመታገዝ ያዘጋጁትን የቡና ችግኞች የተፈጥሮ ማዳበሪያ በመጠቀም መትከላቸውን ተናግረዋል ።

ባለፉት ዓመታት ከተከሉት የቡና ችግኞች ተስፋ ሰጪ ምርት ማግኘት በመጀመራቸው ዘንድሮም በሽታን የመቋቋም አቅም ያላቸው 12 ሺህ ችግኞችን  የተከሉ ሲሆን÷ለተከሏቸው ችግኞችም አስፈላጊውን እንክብካቤ እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የኖኖ ወረዳ አርሶአደር ረቡማ ፈይሳ በበኩላቸው÷ ከመደበኛ ሰብል ልማት ጎን ለጎን በተሻሻለ መንገድ ከ10 ሺህ በላይ የቡና ችግኝ ተተክሏል ማለታቸውን  ኢዜአ ዘግቧል ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version