Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ፖሊስ ከቻይና ፖሊስ ጋር በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ደህንነትን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ገለፀ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት ÷ ጉባኤው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ የትላልቅ ሁነቶች ደህንነት፣ የቪ አይ ፒ ደህንነት፣ ፈጣን ምላሽ መስጫ ስልቶችና የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ላይ ምክክር መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ውይ ይቱ ከቻይና ህዝብ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች ልምድ እና ዕውቀት ለመለዋወጥ  ከፍተኛ እድል መፍጠሩን የተናገሩት ኮሚሽነር ጄኔራሉ÷በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት ባለሙያዎች በማስተባበር መሰል ምክክሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል፡፡

የሴሚናሩ ተሳታፊ የፖሊስ አባላት በልምድ ልውውጡ ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ እንዲያደርግ እና ለሌሎች አባላትም ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

ፌዴራል ፖሊስ ከቻይና የህዝብ ደህንነት ሚኒስቴር ጋር ያለውን ፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ መናገራቸውን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version