Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ መስፍን ጣሰው አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማገናኘት ረገድ ላሳዩት የላቀ አመራርነት ሚና ተሸለሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማገናኘት ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጫወተ ላለው ሚና ላሳዩት የላቀ የአመራርነት ሚና ተሸላሚ ሆነዋል።

በአፍሪካ አህጉር ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና ላይ የሚያተኩረው የ“2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” በጋና አክራ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ አቶ መስፍን ጣሰው አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማገናኘት ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጫወተ ላለው ሚና ላሳዩት የላቀ የአመራርነት ሚና ተሸላሚ ሆነዋል።

ሽልማቱ አፍሪካን እርስ በርስ በማገናኘት ቁርጠኛ የአመራርነት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ዕውቅና የሚሰጥበት ነው ተብሏል፡፡

በ“2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ታላላቅ አህጉር ዓቀፍ የንግድ ተቋማት መሪዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መገኘታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version