አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ካናዳ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚከናወኑ የተለያዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሃሰን ከኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ጆሿ ታባህ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን ፥ በክልሉ ያለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም የሰላም ሁኔታ በተመለከተ ለአምባሳደሩ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ቀደም ሲል በካናዳ መንግስት እየተተገበረ ባለው የልማት ትብብር ፕሮግራም በክልሉ በትምህርትና በሴቶች አቅም ግንባታ እየተደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አምባሳደር ጆሽዋ በበኩላቸው በክልሉ ሰላምን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቅሰው ፥ በክልሉ በሚከናወኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የካናዳ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡