Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚስተዋሉ የፋይናንስ ተደራሽነት ችግሮች እንዲቀረፉ ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚታየው የፋይናንስ ተደራሽነት ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሹ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰመሪታ ሰዋሰው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአሜሪካ ኒዮርክ በተዘጋጀው አራተኛው የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ለልማት ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በጉባኤው ኢትዮጵያን በመወከል ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰመሪታ ሰዋሰው ÷ በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚስተዋሉ የፋይናንስ ተደራሽነት ችግሮች እና የሃብት ኢ-ፍትሃዊነት ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍ ተጨባጭ፣ ፍትሃዊ እና ፈጣን ምለሽ መስጠት የሚችል ሰነድ እንዲዘጋጅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለችግሩ ተግባራዊ መፍትሄ ለማምጣት የተመድ አባል ሀገራት እና ዓለማቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የትርክት እና የእይታ ለውጥ ሊያደርጉ እንደሚገባ መግለፃቸውን የሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ቀደም ሲል በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የሚያጋጥማቸውን የፋይናንስ ተደራሽነት ችግሮች ለመፍታት በዓለም አቀፉ የፋይናንስ ለልማት ኮንፈረንስ ላይ የተፈረሙ ስምምነቶች ተግባራዊ ሊደረጉ እንደሚገባም አሳስበዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡

Exit mobile version