አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአንጎላ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴቴ አንቶኒዮ እና ከኮሞሮስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚባኢ ሞሃመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በተናጠል በተካሄደው ውይይትም በሀገራቱ የሁለትዮሽ፣ ባለብዙ ወገን እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመን ትብብር ለማጠናክር መስማማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ቀድም ሲል በሀገራቱ መካከል በተለያዩ ዘርፎች የተፈረሙ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሱም ተጠቁሟል፡፡