Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓድዋ ድል የአንድነት እና የጽናት ተምሳሌት ነው – ጠ/ሚ ሚያ ሞተሊን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊን የዓድዋ ድል የአንድነትና የጽናት ተምሳሌት ነው ሲሉ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊምን ተቀብለው የዓድዋ ድል መታሰቢያን አስጎበኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሯ በዓድዋ ጀግኖች ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን ያኖሩ ሲሆን መታሰቢያውን በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ የዓድዋ ድል የአንድነት እና የጽናት ተምሳሌት እንዲሁም በትብብር ማንኛውንም ኃይል የማሸነፍ ምልክት መሆኑን መናገራቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡
Exit mobile version