Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዘንድሮው የኅብረቱ ጉባኤ እድገታችንን ከገቱ ስብራቶችና ከታሪካዊ ኢ-ፍታዊነት ቁስል የምንሽርበት መሆን ይገባዋል- ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ እድገታችንን ከገቱ ስብራቶች እና ከታሪካዊ ኢ-ፍታዊነት ቁስል የምንሽርበት መሆን ይገባዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ38ተኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ባደርጉት ንግግር የአፍሪካ ጥሪ የበጎ ፍቃድ ወይም የገንዘብ እርዳታ ሳይሆን የፍትህ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ክብር ለማስመለስ እንዲሁም የድህነትን፣ የእኩልነትን እና የአድልዎን ጥልቅ ጠባሳ መፈወስ ያስፈልጋል ብለዋል።

 

እንዲሁም ከአፍሪካዊያን የሚመዘበሩ የተፈጥሮ ሀብት እና እድሎችን ፍጻሜ ማበጀት ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡

 

ይህን ለማድረግ የደረሱ ጉዳቶችን እውቅና በመስጠት ለወደፊት አፍሪካዊያንን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ጠንካራ ርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አክለውም ለዚህም ከቃላት በዘለለ በተግባር የተደገፉ ተጨባጭ ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

 

 

 

Exit mobile version