Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው።

በዚህ መሰረትም የጋምቢያ ም/ፕሬዚዳንት ሙሐመድ ቢ.ኤስ ጃሎ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና (ዶ/ር)፣ የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ጁሊዬስ ማዳ ቢዮ፣ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ፣ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉህ እና የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፋውስተን አኬንጀ ቱዋዴራ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

 

በተጨማሪም የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ዩማ ቡይካይ፣ የሳሀራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብራሂም ጋሊ፣ የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ፣ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስቴ ዳይሺሚዬ፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ፕሬዚዳንት ካርሎስ ማኑዌል ቪላ ኖቫ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ለመሪዎቹ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የክብር አሸኛኘት ያደረጉላቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version